ከመኪና ሳይወርዱ የኮቪድ-19 (COVID-19) ምርመራ

international community health services Drive-thru Covid-19 Testing Information in Amharic

 

በአሁኑ ሰዓት በሁለት አይ.ሲ.ኤች.ኤስ (ICHS) ቅርንጫፎች ከመኪና ሳይወርዱ የኮቪድ-19 (COVID-19) ምርመራ በቀጠሮ መስጠት ጀምረናል

 

ሰኞ: ዕሮብ: አርብ ከጠዋት 10:00am እስከ ከሰአት 2:00pm

በቀጠሮ ብቻ ስለሆነ በስልክ ቁጥር 206.788.3700 ደውለው ቀጠሮ ይያዙ

ከሰኞ እስከ አርብ; ከጠዋት 11:00am እስከ ከሰአት 3:00pm

በቀጠሮ ብቻ ስለሆነ በስልክ ቁጥር 206.533.2600 ደውለው ቀጠሮ ይያዙ

 

የአገልግሎቱ ክንዋኔ

በቀጠሮዎት ግዜ እርስዎ ከመኪና ውስጥ እንዳሉ የጤና ባለሙያ በመኪናው መስኮት በመቅረብ ከአፍንጫ ውስጥ ናሙና ይወስዳል:: በተጨማሪ የምርመራውን ውጤት እንዴት እንደሚያገኙት ይነግርዎታል:: ለምርመራ በሚመጡበት ግዜ አስተርጏሚ ካስፈለግዎት የአስተርጓሚ አገልግሎት እንሰጣለን::

 

ምርመራ ማግኘት የሚችለው ማነው?

ማንኛውም የህብረተሰብ አካል ይሄን ምርመራ ማግኘት ይችላል:: የግድ የ አይ.ሲ.ኤች.ኤስ (ICHS) ታካሚ መሆን የለብዎትም ግን በቅድሚያ ደውለው ቀጠሮ ማስያዝ አለብዎት:: የመመርመሪያ መሳርያ እጥረት ስላለ በቅድሚያ ምርመራውን የምናደርገው የኮቪድ-19 (COVID-19) ምልክት ለሚያሳዩ ሰዎች ነው:: እነዚህም ትኩሳት: ሳል: የጉሮሮ ህመም እና የትንፋሽ እጥረት ናቸው:: በዚህ ግዜ ምርመራ እንደሚያስፈልግዎት ከተወሰነ ቀጠሮ ይሰጥዎታል::